News and Events

News

የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር

ለአንድ ወር የሚቆይ በማሞግራፊ ምርመራ ላይ የ 50% ቅናሽ ማድረጋችንን ስንገልፅ በደስታ ነዉ

የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር

🌸 የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር 🌸

📌የጡት ካንሰር የሚከሰተው በ genetic abnormality (በዘረ-መል ችግር) ምክንያት ነው። የዘረመል ችግር በዘር የተላለፈ ወይም በዘር ያልተላለፈ ሊሆን ይችላል።

📌ለጡት ካንሰር አጋላጭ የሚያደርጉ ነገሮች
> ማንኛውም ሰው ወንድም ሆነ ሴት በጡት ካንሰር የመያዝ እድል አለው። > በሃገራችን የተደረጉ ጥናቶች ባይኖሩም በሌላው አለም ግን ከ 8 ሴቶች አንዷ በጡት ካንሰር ትያዛለች።

📌የጡት ካንሰር ተጋላጭነት የሚጨምሩ ነገሮች ( risk factors)
- እድሜ (ከ50 አመት በላይ መሆን)
- የተቀየረ ዘረመል ከቤተሰብ መውረስ (BRACA1 & BRACA 2 Gene)
- የተራዘመ የወር አበባ ጊዜ ( ከ 12 አመት በታች የወር አበባ ማየትና የወር አበባ የቆመበት ጊዜ ከ55 አመት በዃላ ሲሆን)
- የጡት የተፈጥሮ አይነት ( በህክምና Dense Breast የምንለው)
- በቤተሰብ ውስጥ የጡት ወይም የእንቁልጢ ካንሰር (Ovarian cancer) ታሪክ መኖር
- ለሌሎች በሽታዎች የሚሰጥ የጨረር ህክምና ( Radiation )
- ከመጠን ያለፈ ውፍረት
- ኤስትሮጅን እና ፕሮጀስትሮን የተባሉ የያዙ መድኃኒቶች መውሰድ
- የመጀመሪያ ልጅን ከ30 አመት በኋላ መውለድ እና ጡት አለማጥባት
- አልኮል መጠጦች ማዘውተር
- ሲጃራ ማጨስ
እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩ ነገሮች ተጋላጭነት ይጨምራሉ ማለት ነው እንጂ ቀጥታ የጡት ካንሰር ያመጣሉ ማለት ግን አይደለም።

ምን ማድረግ አለብን?
🎀 ማስቀረት ወይም መቀነስ የምንችላቸውን ተጋላጭነት የሚጨምሩ ነገሮች ማስተካከል
🎀 በየጊዜው ጡታችንን መፈተሽ ( Breast self examination )
🎀 ከሃኪም ጋር በመመካከር የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራ በየጊዜው ማድረግ ብቸኛ መፍትሄዎች ናቸው።

👉ዘመን አፈራሽ በሆነው ማሞግራፊ መሳሪያችን በመታገዝ የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራ አገልግሎት እንሰጣለን።

👉 ለጥቅምት ወር የሚቆይ በማሞግራፊ ምርመራ ላይ የ 50% ቅናሽ ማድረጋችንን ስንገልፅ በደስታ ነዉ።

👉መተው ይጎብኙን ከበቂ የህክምና ምክር አገልግሎት ጋር አስፈላጊውን ምርመራ አድርገው ይመለሳሉ!!!